ኦሪት ዘፀአት 23
23
ትክክለኛ ፍርድ
1 #
ዘፀ. 20፥16፤ ዘሌ. 19፥11፤12፤ ዘዳ. 5፥20። “ሐሰተኛ ወሬ አታሰራጭ፥ ሐሰተኛ ምስክር ለመሆንም ከኃጢአተኛ ጋር አትተባበር። 2ክፉ ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድንም ለማጣመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር። 3#ዘሌ. 19፥15።በፍርዱ ጊዜ ለድሀው አታድላ። 4#ዘዳ. 22፥1-4።የጠላትህን በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው ለእርሱ መልስለት። 5የሚጠላህን ሰው አህያ ከሸክሙ በታች ወድቆ ብታየው አትተወው፥ ነገር ግን እንዲነሳ እርዳው። 6#ዘሌ. 19፥15፤ ዘዳ. 16፥19።በፍርዱ ጊዜ የድሀውን ፍርድ አታጥምም። 7ከሐሰት ነገር ራቅ፤ ንጹሑንና ጻድቁን አትግደል፥ እኔ ኃጢአተኛውን አላጸድቅምና። 8ጉቦን አትቀበል፤ ጉቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። 9#ዘፀ. 22፥21፤ ዘሌ. 19፥33፤34፤ ዘዳ. 24፥17፤18፤ 27፥19።መጻተኛውን አትጨቁን፤ እናንተ ራሳችሁ በግብጽ ምድር መጻተኞች ስለ ነበራችሁ የመጻተኛ ነፍስ እንዴት እንደ ሆነች ታውቃላችሁና።
ሰባተኛው ዓመትና ሰባተኛው ቀን
10 #
ዘሌ. 25፥1-7። “ስድስት ዓመት ምድርህን ዝራ፥ ምርትዋንም ሰብስብ፤ 11በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህ ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። በወይንህና በወይራህም ላይ እንዲሁ አድርግ። 12#ዘፀ. 20፥9-11፤ 31፥15፤ 34፥21፤ 35፥2፤ ዘሌ. 23፥3፤ ዘዳ. 5፥13፤14።ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ እንዲያርፉ የባርያህ ልጅና መጻተኛውም ዕረፍት እንዲሆንላቸው በሰባተኛው ቀን ዕረፍ። 13የነገርኳችሁን ነገር ሁሉ ጠብቁ፤ የሌሎችን አማልክት ስም አትጥሩ፥ ከአፍህም አይሰማ።
ዓመታዊ በዓላት
14“በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታደርግልኛለህ። 15#ዘፀ. 12፥14-20፤ ዘሌ. 23፥6-8፤ ዘኍ. 28፥17-25።የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ። 16#ዘሌ. 23፥15-21፤ ዘኍ. 28፥26-31፤ ዘሌ. 23፥39-43።የመከር በዓል፥ በእርሻህ የዘራኸውን የፍሬህን በኵራት፥ ዓመቱም ሳያልቅ ፍሬህን ከእርሻ በምትሰበስብበት ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ። 17በዓመት ሦስት ጊዜ ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ። 18የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ ቂጣ ጋር አትሠዋ፤ የበዓሌም ስብ እስከ ንጋት ድረስ አይቆይ። 19#ዘዳ. 26፥2፤ ዘፀ. 34፥26፤ ዘዳ. 14፥21።የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ ጌታ አምላክህ ቤት አምጣ፤ ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።
ቃል የተገባችላቸው ከንዓንን መውረስ
20“በመንገድ እንዲጠብቅህ፥ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ እንዲያስገባህ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እልካለሁ። 21በፊቱ ተጠንቀቅ፥ ቃሉንም አድምጥ፤ ስሜ በእርሱ ስለ ሆነ ብትተላለፉ ይቅር አይልምና አታስመርረው። 22አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጠላለሁ፥ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። 23መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያን፥ ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኤዊያውያንና ወደ እያቡሳውያን ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ። 24ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፥ አታገልግላቸውም፥ እንደ ሥራቸውም አትሥራ፤ ነገር ግን ፈጽመህ አፍርሳቸው፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብራቸው። 25ጌታ አምላካችሁን ታገለግላላችሁ፤ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። 26በምድርህ የምትጨነግፍ ወይም መካን አትኖርም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ። 27መፈራቴን በፊትህ እልካለሁ፥ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደንግጣቸዋለሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ። 28በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፥ ኤዊያዊውንም ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ከፊትህ አባርራለሁ። 29ምድሪቱ ባድማ እንዳትሆን፥ የምድር አራዊትም እንዳይበዙብህ፥ በአንድ ዓመት ውስጥ ከፊትህ አላባርራቸውም። 30እስክትበዛና ምድርንም እስክትወርስ ድረስ በጥቂት በጥቂት አባርራቸዋለሁ። 31ድንበርህንም ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረበዳ እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፥ ከፊትህ ታባርራቸዋለህ። 32ከእነርሱ ጋርና ከአማልክቶቻቸው ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ። 33በምድርህ አይቀመጡ አማልክቶቻቸውን በማገልገል እኔን እንድትበድል ያደርጉሃልና፥ ይህም ለአንተ ወጥመድ ይሆንብሃል።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 23: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ