ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3
3
የጳውሎስ ሥራ ለአሕዛብ
1አሕዛብ ስለ ሆናችሁ ስለ እናንተ ነው እኔ ጳውሎስ ለክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆንኩት። 2በእርግጥ ስለ እናንተ ሲባል ስለ ተሰጠኝ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ መጋቢነት ሰምታችኋል፤ 3አስቀድሜ በአጭሩ እንደ ጻፍሁ፥ ይህን ምሥጢር በመግለጥ አስታወቀኝ፤ 4#ቈላ. 1፥26-27።ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምሥጢር እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ ትችላላችሁ፤ 5ይህ ምስጢር አሁን ለቅዱሳኑ ሐዋሪያትና ለነቢያት በመንፈስ እንደተገለጠው ባለፉት ትውልዶች ለነበሩ አልተገለጠም ነበር። 6ይህ የሆነው፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ ነው።
7ለዚህ ወንጌል በኀይሉ አሠራር እንደተሰጠኝ እንደ የእግዚአብሔር ጸጋ ስጦታ መጠን አገልጋይ ሆንኩ። 8ከቅዱሳን ሁሉ ያነስኩ ብሆንም፥ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጠግነት ለአሕዛብ እንድሰብክ፥ ይህ ጸጋ ለኔ ተሰጠ፤ 9ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘለዓለም የተሰወረው የምሥጢር አሳብ ምን እንደሆነ ለሁሉ እንድገልጥ፥ 10በዚህም ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት እንድትታወቅ ነው። 11ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የፈጸመው የዘለዓለም አሳብ ነበረ። 12በእርሱም ባለን እምነት አማካኝነት በድፍረትና በመተማመን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን። 13ስለዚህ፥ ክብራችሁ ነውና፥ ስለ እናንተ ስለምቀበለው መከራዬ እንዳትታክቱ እለምናችኋለሁ።
የክርስቶስን ፍቅር ስለ ማወቅ
14በዚህም ምክንያት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤ 15ከእርሱም በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ስያሜ ያገኛል። 16እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን፥ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ እጸልያለሁ፤ 17ሥር ሰዳችሁ፥ በፍቅርም ታንጻችሁ ክርስቶስ በልባችሁ በእምነት እንዲኖር፥ 18#ሲራ. 1፥3። ስፋቱና ርዝመቱ፥ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ማስተዋል ላይ እንድትደርሱ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር፥ እጸልያለሁ፤ 19የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ድረስ እንድትሞሉ፥ እውቀትን የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር እንድታውቁ ነው።
20እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው፥ 21ለእርሱ፥ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
Currently Selected:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ