ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በትውልድ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በአካል ላይ በሰው እጅ ከተደረገው የተነሣ፥ “ተገርዘናል” በሚሉት፥ “ያልተገረዛችሁ” የተባላችሁትን ያን አስታውሱ፤ በዚያ ዘመን በዚህም ዓለም ያለ ክርስቶስ ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፥ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፥ ተስፋን አጥታችሁና ከእግዚአብሔር ተለይታችሁ እንደ ነበር አስታውሱ። አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፥ ሁለቱን አንድ ያደረገ፥ እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሕግን ከትእዛዛቱና ከሥርዓቱ ጋር ሻረ፤ ከሁለቱ አንድ አዲስ ሕዝብ ፈጥሮ ሰላምን አደረገ፤
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:11-15
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች