ኦሪት ዘዳግም 3
3
የባሳን ንጉሥ ዖግ መሸነፍ
1 #
ዘኍ. 21፥33-35። “ከዚያ ተመልሰን በባሳን መንገድ ወጣን፥ የባሳን ንጉሥ ዖግም፥ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ፥ በኤድራይ ሊዋጉን ወጡ። 2ጌታም፦ ‘እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁና አትፍራው፥ በሐሴቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግህ በእርሱም ታደርግበታለህ’ አለኝ።”
3ስለዚህ ጌታ አምላካችን ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዖግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፥ እኛም አንድ ሰው እንኳ ሳናስቀርለት አጠፋነው። 4ያን ጊዜም ከተሞቹ ሁሉ ያዝን፥ የአርጎብን ግዛቶች ሁሉ፥ ከሥልሳ ከተሞች ጋር፥ በባሳን ያለውን የዖግን መንግሥት፥ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም። 5እነዚህ ሁሉ ከተሞች፥ በቅጥር ካልተመሸጉት ከእጅግ ብዙ ከተሞች ሌላ፥ ቁመቱ ረጅም በሆነ ቅጥር በመዝጊያና በመወርወሪያም የተመሸጉ ነበሩ። 6#ዘዳ. 2፥34-35፤ 7፥2፤ 26፤ 13፥16፤ 18፤ 20፥16-18፤ ኢያ. 10፥40፤ 11፥11-12።በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ፈጽሞ ደመሰስናቸው፥ እያንዳንዱን ከተማ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችና ሕፃናት ሁሉ አጠፋናቸው። 7ከብቶቹን ሁሉ የከተሞቹንም ምርኮ ለራሳችን ዘረፍን።
8በዚያን ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩት ሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት እጅ፥ ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ሔርሞን ተራራ ድረስ፥ ምድሪቱን ወሰድን። 9የሔርሞንን ተራራ ሲዶናውያን ሢርዮን ብለው ሲጠሩት፥ አሞራውያን “ሠኒር” ብለው ሰይመውታል። 10በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ ባሳንን ሁሉ፥ እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ድረስ፥ በባሳንም ያሉትን የዖግን መንግሥት ከተሞች ወሰድን። 11#ዘዳ. 2፥11፤ 20፤ 3፥13፤ ዘፍ. 14፥5፤ 15፥20፤ ኢያ. 12፥4፤ 13፥12፤ 17፥15።ከራፋያውያን ወገን የባሳን ንጉሥ ዖግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፥ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በራባት አለ፥ ቁመቱ ዘጠኝ ክንድ የጎኑም ስፋት አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።
12 #
ዘኍ. 32፥1-42፤ ኢያ. 13፥8-33። በዚያን ወቅት ይህችን ምድር በወረስን ጊዜ፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ አገር እኩሌታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠኋቸው። 13#ዘዳ. 2፥11፤ 20፤ 3፥11፤ ዘፍ. 14፥5፤ 15፥20፤ ኢያ. 12፥4፤ 13፥12፤ 17፥15።ከገለዓድም የቀረውን የዖግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ግዛት ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፥ ያቺ ባሳን ሁሉ የራፋይም አገር ተብላ ተጠራች። 14#ዘኍ. 32፥41፤ መሳ. 10፥4፤ 1ዜ.መ. 2፥23።የምናሴ ልጅ ያኢር፥ ባሳንን እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ፥ የአርጎብን ግዛት ሁሉ ወሰደ፥ ይችንም የባሳን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በሚጠራበት የያኢር መንደሮች ብሎ ጠራ። 15ለማኪርም ገልዓድን ሰጠሁት። 16ለሮቤልና ለጋድም ነገዶች ከገለዓድ ጀምሮ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ፥ የሸለቆውን አማካይ እንደ ወሰን፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ሰጠሁ፤ 17ዓረባንም፥ ከዮርዳኖስ ጋር እንደ ወሰን፥ ከኪኔሬት እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ፥ የጨው ባሕር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ ያለውን ያካትታል።
18 #
ኢያ. 1፥12-15፤ 4፥12፤ 22፥1-4። በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ። 19ነገር ግን፥ ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁ አውቃለሁና፥ ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀራሉ፤ 20ይኸውም ጌታ እናንተን እንዳሳረፈ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁሉ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።”
21ኢያሱንም ያንጊዜ አዘዝኩት፦ “ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፥ እንዲሁ ሁሉ በምታልፍባቸው መንግሥታት ላይ ጌታ ያደርጋል። 22#ዘዳ. 1፥30፤ ዘፀ. 14፥13-14።ጌታ አምላካችሁ እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋልና አትፍሯቸው።”
ሙሴ ወደ ከነዓን እንዳይገባ መከልከሉ
23 #
ዘኍ. 27፥12-23። “በዚያን ጊዜ ለጌታ እኔ እንዲህ ብዬ ለመንሁ፦ 24‘ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህን የጸናችውንም እጅህን ለእኔ ለአገልጋይህ ማሳየት ጀምረሃል፥ በሰማይም ሆነ በምድርም እነዚህ ሥራዎችና ኃያል ተግባራት እንደ አንተ ማድረግ የሚችል አምላክ ማን ነው? 25እለምንሃለሁ፥ ልሻገር፥ በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።’
26 #
ዘዳ. 4፥21። “ጌታ ግን በእናንተ ምክንያት ተቆጥቶኝ ነበር፥ አልሰማኝምም፥ ጌታም አለኝ፦ ‘እንግዲህ ይበቃሃል፤ በዚህ ጉዳይ ዳግመኛ አትናገረኝ። 27#ዘዳ. 3፥17፤ 32፥48-52፤ 34፥1-4።ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ፒስጋ ራስ ውጣ፥ ዓይንህንም አንሥተህ ወደ ምዕራብና ሰሜንም ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም በዓይንህ ተመልከት። 28#ዘዳ. 1፥38፤ 31፥7-8።ይልቅስ ኢያሱን እዘዘው፥ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻገራልና፥ አንተም የምታያትን ምድር እርሱ ያወርሳቸዋልና፥ አደፋፍረውም፥ አበርታውም።’
29“እኛም በቤተፌዖር ፊት ለፊት በሸለቆው ውስጥ ተቀመጥን።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 3: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ