ኦሪት ዘዳግም 19:10-12

ኦሪት ዘዳግም 19:10-12 መቅካእኤ

ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር የንጹሕ ሰው ደም እንዳይፈስና በሚፈሰውም ደም በደለኛ እንዳትሆን ይህን አድርግ። “ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፥ አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፥ ቢገድለውና፥ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥ የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፤ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት።