የሐዋርያት ሥራ 7:9-16

የሐዋርያት ሥራ 7:9-16 መቅካእኤ

“የአባቶችም አለቆች በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብጽ ሸጡት፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ከመከራውም ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብጽና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው። በግብጽና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፤ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም። ያዕቆብም በግብጽ እህል መኖሩን በሰማ ጊዜ በመጀመሪያ አባቶቻችንን ሰደዳቸው፤ በሁለተኛውም ዮሴፍ ለወንድሞቹ ታወቀ፤ የዮሴፍም ትውልድ በፈርዖን ዘንድ ተገለጠ። ዮሴፍም አባቱን ያዕቆብንና ሰባ አምስት ነፍስ የነበረውን ቤተ ዘመድ ሁሉ ልኮ አስጠራ። ያዕቆብም ወደ ግብጽ ወረደ፤ እርሱም ሞተ፤ አባቶቻችንም፤ ወደ ሴኬምም አፍልሰው አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር በገዛው መቃብር ቀበሩአቸው።