የሐዋርያት ሥራ 28:23-24

የሐዋርያት ሥራ 28:23-24 መቅካእኤ

ቀንም ቀጥረውለት ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያው ወደ እርሱ መጡ፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየመሰከረ ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት ጠቅሶ እያስረዳቸው፥ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ይገልጥላቸው ነበር። እኩሌቶቹም የተናገረውን አመኑ፤ እኩሌቶቹ ግን አላመኑም፤