የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

3ኛ የዮሐንስ መልእክት 1

1
ሰላምታ
1 # የሐዋ. 19፥29፤ ሮሜ 16፥23፤ 1ቆሮ. 1፥14። ሽማግሌው፥ በእውነት ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ።
2ወዳጄ ሆይ! በመንፈስ እንዳደግህ ሁሉ፥ በነገር ሁሉ እንዲሳካልህና በመልካም ጤንነት እንድትኖር እጸልያለሁ። 3ወንድሞች መጥተው በአንተ ስላለው እውነትና አንተም በእውነት እንደምትመላለስ ሲመሰክሩልኝ እጅግ ደስ አለኝ። 4ልጆቼ በእውነት እንደሚመላለሱ ከመስማት የሚበልጥ ደስታ የለኝም።
የጋይዮስ መመስገን
5ወዳጄ ሆይ! ምንም እንኳ እንግዶች ቢሆኑም ለወንድሞች የምታደርገውን ነገር ሁሉ በታማኝነት ታደርጋለህ፤ 6እነርሱም በቤተ ክርስቲያን ፊት ስለ ፍቅርህ መስክረዋል፤ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳቸው መልካም ታደርጋለህ፤ 7ስለ ስሙ ብለው፥ ከአሕዛብ ምንም ሳይቀበሉ ወጥተዋልና። 8ስለዚህ የእውነት የሥራ ተባባሪዎች እንድንሆን እንደነዚህ ያሉትን ልንቀበል ይገባናል።
ዲዮጥራፊስና ድሜጥሮስ
9ለቤተ ክርስቲያን አንድ ነገር ጽፌ ነበር፤ ነገር ግን መሪ ለመሆን የሚፈልገው ዲዮጥራፊስ አልተቀበለንም። 10ስለዚህ እኔ ከመጣሁ፥ ስለ እኛ የተናገረውን ክፉ ቃል፥ የሠራውን ሥራ አሳስበዋለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፤ ሊቀበሉአቸው የሚፈልጉትን ይከለክላቸዋል፥ ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።
11ወዳጄ ሆይ! መልካሙን እንጂ ክፉን አትምሰል። መልካም የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም። 12ድሜጥሮስ በሁሉም ተመስክሮለታል፤ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም እንመሰክርለታለን፤ ምስክርነታችን ደግሞ እውነት እንደሆነ ታውቃለህ።
የመጨረሻ ሰላምታ
13የምጽፈው ብዙ ነገር ነበረኝ፥ ነገር ግን በቀለምና በብርዕ ልጽፍልህ አልወደድሁም፤ 14ነገር ግን ወዲያው ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ፊት ለፊት እንነጋገራለን።
15ሰላም ለአንተ ይሁን። ወዳጆች ሰላም ይሉሃል። ወዳጆችን በየስማቸው ሰላም በልልኝ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ