የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2

2
የዓመፅ ሰው
1 # 1ተሰ. 4፥15-17። ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን ይህን እንለምናችኋለን፤ 2ከእኛ በሚመስል መልእክት ወይም በቃል ወይም በመንፈስ፦ “የጌታ ቀን መጥቷል፤” ብላችሁ አእምሮአችሁ በቀላሉ አይናወጥ አይደንግጥም። 3ማንም ሰው በማናቸውም መንገድ አያታልላችሁ፤ ከሐዲው አስቀድሞ ሳይመጣ የዓመፅም ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና። 4#ዳን. 11፥36፤ ሕዝ. 28፥2።እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል። 5ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችሁ እንደ ነበረ አታስታውሱምን? 6አሁን ምን እንደከለከለው አውቃችኋልና በራሱ ጊዜ የተገለጠ ይሆናል። 7አስቀድሞም የዓመፅ ሚስጢር በሥራ ላይ ነው፤ አሁን ግን እርሱ ብቻ ይከለክለዋል፤ እርሱም እንዲህ የሚያደርገው ከመንገድ እስከሚወገድ ድረስ ነው። 8#ኢሳ. 11፥4።በዚያም ጊዜ ዓመፀኛው ይገለጣል፤ ጌታ ኢየሱስም በአፉ እስትንፋስ ይገድለዋል፤ በመምጣቱም መገለጥ ያጠፋዋል፤ 9#ማቴ. 24፥24።ዓመፀኛው ከሙሉ ኃይልና ምልክቶች፥ ከሐሰትም ተአምራቶች ጋር ሆኖ በሰይጣን አሠራር ይመጣል። 10እንዲሁም ለመዳን እውነቱን ወድደው ባለ መቀበላቸው ለሚጠፉት በማታለል ክፋት ሁሉ ይመጣባቸዋል። 11ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የሐሰትን ኑፋቄ በመላክ በስሕተት እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል። 12በዚህም እውነቱን ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ የሚሰኙ ሁሉ ይፈረድባቸዋል።
ለመዳን የተመረጡ ሰዎች
13በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው አንሥቶ በመንፈስ በመቀደስና በእውነት በማመን እንድትድኑ መርጦአችኋልና፤ 14ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ። 15ስለዚህም ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ትውፊት ያዙ።
16ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና፥ የወደደን በጸጋም የዘለዓለምን መጽናናትና መልካሙን ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን 17ልባችሁን ያጽናናው፥ በቃልና በመልካም ሥራ ሁሉ ያጽናላችሁም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ