የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1:7-10

2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1:7-10 መቅካእኤ

እንዲሁም እርሱ ጌታ ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል በሚመጣበት ጊዜ መከራን ለተቀበላችሁት ከእኛ ጋር ዕረፍትን ይሰጣችኋል፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤ ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘለዓለም ጥፋት ይቀጣሉ። ይህም የሚሆነው ምስክርነታችን በእናንተ በመታመኑ የተነሣ ባመኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅና፥ በቅዱሳኑም ሊከብር በሚመጣበት ጊዜ በዚያ ቀን ነው።