2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6
6
ታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ
1 #
1ዜ.መ. 13፥1-14። ዳዊት እንደገና ከእስራኤል የተመረጡትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች ሰበሰበ። 2#ዘፀ. 25፥10፤ ኢያ. 15፥9፤ 1ዜ.መ. 13፥6፤ መዝ. 132፥8-10።ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው በዓል ሄዱ። 3#1ሳሙ. 4፥3-4፤ 6፥7-8፤ 7፥1፤ ዳን. 3፥55።የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው፥ በኰረብታ ላይ ካሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም የአቢናዳብ ልጆች ዖዛና አሒዮ ነበሩ፤ 4የእግዚአብሔርም ታቦት በሠረገላው ላይ ሆኖ፥ አሒዮ ፊት ፊት ይሄድ ነበር። 5#መዝ. 68፥24-25፤ 150፥3-5።ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ በዝማሬ፥ በበገና፥ በመሰንቆ፥ በከበሮ፥ በጽናጽልና በቃጭል ድምፅ በጌታ ፊት ያሸበሽቡ ነበር።
6ወደ ናኮን አውድማ ሲደርሱም በሬዎቹ ስለተደናቀፉ፥ ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ። 7ዖዛ በድፍረት ይህን ስላደረገ፥ የጌታ ቁጣ በላዩ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀሠፈው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ እዚያው ሞተ። 8የጌታ ቁጣ ዖዛን ስለሰበረው ዳዊት አዘነ፤ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ፌሬጽ ዑዛ#6፥8 በዕብራይስጥ የዑዛ ስብራት ማለት ነው። ተብሎ ይጠራል። 9ዳዊት በዚያን ቀን ጌታን ስለ ፈራ “የጌታ ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?” አለ። 10ስለዚህ ዳዊት የጌታን ታቦት አብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ ዖቤድ ኤዶም ቤት ወሰደው። 11#1ዜ.መ. 26፥4።የጌታም ታቦት የጌት ሰው በሆነው በዖቤድ ኤዶም ቤት ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ጌታም ዖቤድ ኤዶምና ቤተሰቡን ሁሉ ባረከ።
12 #
1ዜ.መ. 15፥1-29፤ መዝ. 24፥7-10። በዚህ ጊዜ፥ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የዖቤድ ኤዶም ቤተሰቡና ያለውን ሁሉ ጌታ ባረከለት” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት ወደዚያው ወርዶ፥ የእግዚአብሔርን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በታላቅ ደስታ አመጣው።#1ነገ. 8፥1። 13እነዚያ የጌታን ታቦት ተሸክመው የነበሩት ሰዎች ስድስት ርምጃ በሄዱ ቍጥር፥ በሬና የሰባ ፍሪዳ ይሠዋ ነበር። 14#1ሳሙ. 2፥18።ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ#6፥14 ከበፍታ የተሠራ ሽርጥ። በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኀይሉ በጌታ ፊት ይጨፍር ነበር። 15እንዲህ ባለ ሁኔታም ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት እየጨፈሩና ቀንደ መለከቱን እየነፉ የጌታን ታቦት አመጡ።
16የጌታ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ፥ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ትመለከት ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት በጌታ ፊት ሲዘልና ሲያሸበሽብ ባየችው ጊዜ በልቧ ናቀችው። 17#ዘሌ. 1፥1-17፤ 3፥1-17፤ 1ዜ.መ. 16፥1-3።ከዚያም የጌታን ታቦት አምጥተው፥ ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ በተዘጋጀለት ስፍራ አኖሩት፤ ዳዊትም የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ። 18ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ ስም ባረከ። 19የእስራኤል ወገን ለሆነው ለሕዝቡ ሁሉ፥ ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እንጀራ፥ አንዳንድ ቁራጭ ሥጋና አንዳንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ ሰጠ፤ ከዚህ በኋላ ሁሉም ወደየቤቱ ሄደ።
20 #
1ዜ.መ. 16፥43። ዳዊትም ቤተሰቡን ለመመረቅ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ግን ልትቀበለው ወጣችና፥ “ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ አንድ ተራ ሰው ራቁቱን መታየቱ ክብሩ ሆኖ ነው!” አለችው። 21#1ሳሙ. 13፥14፤ 15፥28።ዳዊትም ሜልኮልን እንዲህ አላት፤ “አዎን ያሸበሸብኩት በጌታ ፊት ነው፤ በአባትሽና በቤቱ ካሉት ሁሉ አስበልጦ በጌታ ሕዝብ በእስራኤል ላይ ገዥ አድርጎ በመረጠኝ በጌታ ፊት አሁንም እጨፍራለሁ። 22እንዲያውም ከዚህ ይልቅ ራሴን በፊቱ ዝቅ አደርጋለሁ፤ ከዚህም የባሰ በፊትሽ የተናቅሁ እሆናለሁ፤ ነገር ግን በጠቀስሻቸው ገረዶች ፊት እከብራለሁ።” 23የሳኦልም ልጅ ሜልኮል እሰከሞተችበት ጊዜ ድረስ ልጅ አልወለደችም ነበር።
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ