የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:15-22

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:15-22 መቅካእኤ

በዚህም እርግጠኛ ስለነበርኩ፥ በእጥፍ እንድትጠቀሙ አስቀድሜ ወደ እናንተ መምጣት ፈልጌ ነበር። ወደ መቄዶንያ ስሄድ በእናንተ በኩል አድርጌ ልጐበኛችሁና፥ ከመቄዶንያም በእናንተ በኩል ተመልሼ ወደ ይሁዳ እንድትልኩኝ ዐቅጄ ነበር። ይህን ማድረግ በመፈለጌ የተከፈለ ሐሳብ አሳይቼ ይሆን? ወይስ በእኔ ዘንድ “አዎን፥ አዎን” እና “አይደለም፥ አይደለም” ማለት እንዲሁ በሰብአዊ መመዘኛ በልማድ ይሆን? እግዚአብሔር የታመነ የሆነውን ያህል በእርግጥ እኛ ለእናንተ የምንናገረው ቃል “አዎን” እና “አይደለም” አይሆንም። ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ፥ እኔም፥ በመካከላችሁ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ “አዎን” እና “አይደለም” አልነበረም፤ ነገር ግን በእርሱ ሁልጊዜ “አዎን” ሆኖአል። እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ “አዎን” ማለት የእርሱ ነው፤ ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር ክብር በእኛ ስለሚነገረው “አሜን” የምንለው እርሱ በኩል ነው። ነገር ግን በክርስቶስ ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፤ ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።