2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 27
27
ኢዮአታም መንገሡ
1ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሳዶቅ ልጅ ኢየሩሳ ትባል ነበር። 2አባቱም ዖዝያን እንዳደረገ ሁሉ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ወደ ጌታ መቅደስ አልገባም፤ ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር። 3የጌታን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፥ በዖፌልም ቅጥር ላይ መጠነ ሰፊ ግንብ ገነባ። 4በተራራማውም በይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን ሠራ፥ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ፥ 5ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ አሸነፋአቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆች በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ተመሳሳ መጠን ያለውን ግብር ገበሩለት። 6ኢዮአታምም በአምላኩ በጌታ ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ። 7የቀረውም የኢዮአታም ነገር፥ ያደረገውም ጦርነት ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። 8መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ። 9ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት፤ ልጁም አካዝ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 27: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ