1ኛ መጽሐፈ ነገሥት መግቢያ
መግቢያ
የመጽሐፉ ስያሜ የተገኘው ከዕብራውያን ትውፊት ሲሆን እነርሱ ይህንን መጽሐፍ በቋንቋቸው “ነገሥት” ብለው ይጠሩት ነበር። መጽሐፈ ነገሥት አንደኛ እና ሁለተኛ አንድ ወጥ መጽሐፎች ነበሩ። መጽሐፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት የተከፈለው የሰብዓ ሊቃናት ተርጓሚዎች በዕብራይስጥ ቋንቋ ተጽፎ የነበረውን ወደ ግሪክ ቋንቋ በተረጐሙበት ጊዜ ነበር። ከዚያ በኋላ የታተሙት መጽሐፎችም ይህንን አከፋፈል ተከትለውታል።
መጽሐፉ እንዲጻፍ ምክንያት ከሆኑት ዋና ዋና ነገሮች መካከል፥ በመጽሐፈ ሳሙኤል ተጀምሮ የነበረውን የእስራኤልን ታሪክ የተሟላ ማድረግ አንዱ ነው፤ እስራኤላውያን በደረሰባቸው ጥፋት፥ ማለትም፦ ከሀገራቸው በመባረራቸውና በመማረካቸው አዝነው “እግዚአብሔር ትቶናል” ብለው አስበው ነበር። ጸሐፊው ግን እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ረስቶ እንዳልተዋቸው፥ ነገር ግን የእስራኤል ነገሥታትና ሕዝቡ እግዚአብሔን ትተውት እንደ ነበር፥ በዚህም ምክንያት ይህ ሁሉ መከራ እንደመጣባቸው ያስገነዝባል።
የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት
የንጉሥ ዳዊት የመጨርሻ ዘመን (1፥1—2፥46)
የንጉሥ ሰሎሞንና ሥራዎቹ (3፥1—11፥43)
የእስራኤል መንግሥት ለሁለት መከፈል (12፥1—22፥54)
ምዕራፍ
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ነገሥት መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ