1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5:9-13

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5:9-13 መቅካእኤ

የሰውን ምስክርነት የምንቀበል ከሆነ የእግዚአብሔር ምስክርነት ይበልጣል፤ እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረው ምስክርነት ይህ ነውና። በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በራሱ ምስክር አለው፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። ምስክርነቱ ይህ ነው፦ እግዚአብሔር የዘለዓለምን ሕይወት ሰጠን፥ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ግን ሕይወት የለውም። በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፥ የዘለዓለም ሕይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ይህን ጽፌላችኋለሁ።