የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 24

24
የካህናቱ አከፋፈል
1የአሮንም ልጆች አመዳደብ ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ። 2#ዘሌ. 10፥1፤2።ናዳብና አብዩድ ግን ልጆች ሳይወልዱ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ አልዓዛርና ኢታምርም ካህናት ሆኑ። 3ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዓርት ከፍሎ መደባቸው። 4የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ዐሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ። 5ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የመቅደሱና በእግዚአብሔር የተሾሙ አለቆች#24፥5 ጥያቄ ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ። 6ከሌዊያውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምንቱ ፊት፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ተመረጠ።
7መጀመሪያውም ዕጣ ለዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ለዮዳኤ፥ 8ሦስተኛው ለካሪም፥ አራተኛው ለሥዖሪም፥ 9አምስተኛው ለመልክያ፥ ስድስተኛው ለሚያሚን፥ 10ሰባተኛው ለአቆስ፥ ስምንተኛው ለአብያ፥ 11ዘጠኝኛው ለኢያሱ፥ አሥረኛው ለሴኬንያ፥ 12ዐሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፥ ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂን፥ 13ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፥ ዐሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፥ 14ዐሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፥ ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፥ 15ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፥ ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፥ 16ዐሥራ ዘጠኝኛው ለፈታያ፥ ሀያኛው ለኤዜቄል፥ 17ሀያ አንደኛው ለያኪን፥ ሀያ ሁለተኛው ለጋሙል፥ 18ሀያ ሦስተኛው ለድላያ፥ ሀያ አራተኛው ለመዓዝያ ዕጣ ወጣ። 19የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዓት ወደ ጌታ ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዓት ይህ ነበረ።
ሌሎች ሌዋውያን
20ከቀሩትም የሌዊ ልጆች፤ ከእንበረም ልጆች ሱባኤል፤ ከሱባኤል ልጆች ዬሕድያ፤ 21ከዓረብያ፤ የዓረብያ ልጆች አለቃው ይሺያ፤ 22ከይስዓራውያን ሰሎሚት፤ ከሰሎሚት ልጆች ያሐት ነበረ፤ 23ከኬብሮንም ልጆች አለቃው ይሪያ፥ ሁለተኛው አማርያ፥ ሦስተኛው የሕዚኤል፥ አራተኛ ይቀምዓም ነበሩ፤ 24የዑዝኤል ልጅ ሚካ፤ ከሚካ ልጆች ሻሚር ነበረ፤ 25የሚካ ወንድም ይሺያ፤ ከይሺያ ልጆች ዘካሪያስ ነበረ፤ 26የሜራሪ ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ፤ ከያዝያ ልጆች በኖ ነበረ፤ 27የሜራሪ ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፥ ሾሃም፥ ዘኩር፥ ዔብሪ ነበሩ፤ 28ከሞሖሊ አልዓዛር፥ እርሱም ልጆች አልነበሩትም፤ 29ከቂስ፤ የቂስ ልጅ ይረሕምኤል ነበረ፤ 30የሙሲም ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ዔደር፥ ኢያሪሙት ነበሩ። እነዚህም እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ። 31እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላቁም እንደ ታናሹ፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ