የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16

16
ታቦቱ በመገናኛ ድንኳን ውስጥ መቀመጡ
1የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕትም በጌታ ፊት አቀረቡ። 2ዳዊትም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት አቅርቦ በፈጸመ ጊዜ በጌታ ስም ሕዝቡን ባረከ። 3ለእስራኤልም ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ አንዳንድ እንጀራ፥ አንዳንድም ቁራጭ ሥጋ፥ አንዳንድም የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ።
4በጌታም ታቦት ፊት እንዲያገለግሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ጌታን እንዲወድሱት፥ እንዲያመሰግኑትና እንዲያከብሩትም ከሌዋውያን ወገን ሾመ። 5አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ መሰንቆና በገና ይጫወቱ የነበሩት ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድ-ኤዶም፥ ይዒኤል ነበሩ፤ አሳፍም የጸናጽልን ድምፅ ያሰማ ነበረ። 6ካህናቱም በናያስና የሕዚኤል በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ሁልጊዜ መለከት ይነፉ ነበር።
የዳዊት የምስጋና ዝማሬ
7በዚያም ቀን ዳዊት በአሳፍና በወንድሞቹ አንደበት ጌታን እንዲያመሰግኑ አስቀድሞ ትእዛዝን ሰጠ።
8ጌታን አመስግኑ፥ ስሙን ጥሩ፤ ለአሕዛብ ሥራውን አውሩ።
9ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤
ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
10በቅዱስ ስሙ ክብር ይሁን፤
ጌታን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
11ጌታን ፈልጉት፥ ብርታቱን እሹ፤
ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
12ተአምራቱንም የተናገረውንም ፍርድ፥
የሠራትን ድንቅ አስቡ፤ እናንተ
13ባርያዎቹ የሆናችሁ የእስራኤል ዘር ሆይ!
ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ!
14እርሱ ጌታ አምላካችን ነው፤
ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።
15ቃል ኪዳኑን ለዘለዓለም፥
እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥
16 # ዘፍ. 12፥7፤ ዘፍ. 26፥3። ለአብርሃም ያደረገውን፥
ለይስሐቅም የማለውን፤
17 # ዘፍ. 28፥13። ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን
ለእስራኤልም የዘለዓለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፤
18እንዲህም አለ፦ “ለአንተ የከነዓንን ምድር
የርስታችሁን ድርሻ እሰጣለሁ፤”
19ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥
እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች በነበሩ ጊዜ ነው።
20ከአንድ ሕዝብ ወደ ሌላ ሕዝብ፥
ከአንድም መንግሥት ወደ ሌላ ሕዝብ ተንከራተቱ።
21 # ዘፍ. 20፥3-7። ማንም ሰው ግፍ እንዲያደርግባቸው አልፈቀደም፤
ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።
22እንዲህም አለ፦ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤
በነቢያቴ ክፉ አታድርጉ።”
23ምድር ሁሉ ጌታን አመስግኑ፤
ዕለት ዕለት ማዳኑን አውሩ።
24ክብሩን ለአሕዛብ፥
ተአምራቱንም ለሰዎች ሁሉ ንገሩ።
25ጌታ ታላቅ፥ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋልና፤
ከአማልክትም ሁሉ በላይ የተፈራ ነው።
26የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤
ጌታ ግን ሰማያትን ሠራ።
27ክብርና ግርማ በፊቱ፥
ኃይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው።
28የአሕዛብ ወገኖች ለጌታ የሚገባውን ስጡ፥
ለጌታ ተገቢውን ክብርና ኃይል ስጡ።
29ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር ስጡ፤
ቁርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤
በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
30ምድር ሁሉ በፊቱ ትናወጥ፤
ዓለሙም ፍጹም እንዳይናወጥ በጽኑ ይታነጻል።
31ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፤
በአሕዛብም መካከል፦ “ጌታ ነግሷል” ይበሉ።
32ባሕርና ሞላዋ በጩኽት ያስገምግሙ፤#16፥32 ሁካታን ያንሡ፤ እሪ ይበሉ፤
በረሀ በእርሷም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ።
33በምድር ሊፈርድ ይመጣልና፥
የዱር ዛፎች በዚያን ጊዜ በጌታ ፊት ደስ ይላቸዋል።
34 # 2ዜ.መ. 5፥13፤ 7፥3፤ ዕዝ. 3፥11፤ መዝ. 99፥5፤ 105፥1፤ 106፥1፤ 117፥1፤ 135፥1፤ ኤር. 40፥11። መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና
ጌታን አመስግኑ።
35እንዲህም በሉ፦ “የመዳናችን አምላክ ሆይ! አድነን፤
ቅዱስ ስምህን እንድናመሰግን፥
በምስጋናህም እንድንከብር፥
ከአሕዛብ መካከል ሰብስበኸን ታደገን።
36ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም፥
የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።”
ሕዝቡም ሁሉ “አሜን” አሉ፤ ጌታንም አመሰገኑ።
ዘውትር የሚደረገው አምልኮ አለመቋረጡ
37እንዲሁም ንጉሥ ዳዊት በየቀኑ እንደሚገባቸው በታቦቱ ፊት ዘወትር እንዲያገለግሉ አሳፍንና ወንድሞቹን፥ ዖቤድ-ኤዶምንም፥ ስልሳ ስምንቱንም ወንድሞቻቸውን በዚያ በጌታ ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
38የኤዶታምም ልጅ ዖቤድ-ኤዶምና ሖሳ የደጁ ጠባቂዎች እንዲሆኑ አድርጎ ከስልሳ ስምንት ወድሞቹ ጋር ዖቤድ-ኤዶምን በዚያ ተወው። 39ካህኑን ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በጌታ ማደሪያ ፊት እንዲያገለግሉ በዚያ ተዋቸው፤ 40በዚያም ለእስራኤልም ባዘዘው በጌታ ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለጌታ ያቀርባሉ። 41ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን እንዲያመሰግኑ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸውም የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር በዚያ ተዋቸው። 42ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታምም ልጆች ጠባቂዎች ነበሩ። 43#2ሳሙ. 6፥19፤20።ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊትም ቤተሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ