መጽሐፈ ሩት 1:19-22

መጽሐፈ ሩት 1:19-22 አማ05

ስለዚህ ሁለቱም አብረው ወደ ቤተልሔም ተጓዙ፤ ቤተልሔም ሲደርሱም የከተማው ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፤ እዚያም ያሉ ሴቶች በመደነቅ “በእርግጥ ይህች ናዖሚ ናትን?” አሉ። እርስዋም እንዲህ አለች፦ “ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን መራራ ስላደረገው ‘ማራ’ በሉኝ እንጂ ‘ናዖሚ’ ብላችሁ አትጥሩኝ፤ ከዚህ አገር በሄድሁ ጊዜ ብዙ ነገር ነበረኝ፤ እግዚአብሔር ግን ባዶ እጄን መልሶኛል፤ ታዲያ ሁሉን የሚችል አምላክ ሲፈርድብኝና ይህን ሁሉ ችግር ሲያደርስብኝ ‘ናዖሚ’ ብላችሁ ለምን ትጠሩኛላችሁ?” እንግዲህ ናዖሚ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር ከሞአብ አገር የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር፤ እነርሱ ቤተልሔም በደረሱ ጊዜ የገብስ መከር የሚሰበሰብበት ወቅት መጀመሩ ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}