የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮም ሰዎች 15:5-13

ወደ ሮም ሰዎች 15:5-13 አማ05

የትዕግሥትና የመጽናናት አምላክ እርስ በርሳችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ በመከተል አብሮ የመኖርን ኅብረት ይስጣችሁ። እንዲሁም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር በአንድ ልብና በአንድ ቃል እንድታከብሩት ያድርጋችሁ። ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ክብር እናንተን እንደ ተቀበላችሁ እናንተ ሁላችሁም አንዱ ሌላውን በደስታ ይቀበለው። ይህንንም ስናገር እግዚአብሔር ለቀደሙት አባቶች የሰጠው ተስፋ እንዲፈጸምና የእግዚአብሔርም እውነተኛነት እንዲታወቅ ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ ሆነ ማለቴ ነው። ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ የሆነበትም ሌላው ምክንያት አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ እንዲያመሰግኑት ነው፤ ይህም፦ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም በዝማሬ ምስጋና አቀርባለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። ደግሞም፥ “እናንተ አሕዛብ፥ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ!” ተብሎ ተጽፎአል። እንደገናም፦ “አሕዛብ ሁሉ! ጌታን አመስግኑት፤ ሕዝቦች ሁሉ አመስግኑት!” ተብሎ ተጽፎአል። እንዲሁም ኢሳይያስ፦ “ከእሴይ ዘር የሚወለድ ይመጣል፤ የአሕዛብም መሪ ለመሆን ይነሣል፤ እነርሱም ተስፋቸውን በእርሱ ላይ ያደርጋሉ” ይላል። ተስፋችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እያደገ እንዲሄድ የተስፋ አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ።