ወደ ሮም ሰዎች 15:15-17

ወደ ሮም ሰዎች 15:15-17 አማ05

አንዳንድ ነገሮችን ላስታውሳችሁ ፈልጌ ይህን መልእክት እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መሠረት በድፍረት ጻፍኩላችሁ። ይህም ጸጋ የተሰጠኝ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለአሕዛብ በማብሠር እንደ ካህን ሆኜ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ነው፤ ስለዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ አገለግላለሁ። በዚህ ምክንያት በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን ለማገልገል በመቻሌ እመካለሁ።