መጽሐፈ መዝሙር 84:10-12

መጽሐፈ መዝሙር 84:10-12 አማ05

በሌላ ስፍራ አንድ ሺህ ቀን ከመቈየት በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው፤ በክፉዎች ቤት ከምኖር ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት ዘበኛ ሆኜ መኖርን እመርጣለሁ። ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም። የሠራዊት አምላክ ሆይ! በአንተ የሚታመኑ እንዴት የተባረኩ ናቸው!