መጽሐፈ መዝሙር 73:1-12

መጽሐፈ መዝሙር 73:1-12 አማ05

ልባቸው ንጹሕ ለሆነ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ቸር ነው። በእኔ በኩል ግን እርምጃዎቼ እየተንገዳገዱ፥ እግሮቼም ሊንሸራተቱ ተቃርበዋል። ይህም የሆነው ትዕቢተኞችና ክፉዎች ሰዎች ሲበለጽጉ በማየቴ ቅናት አድሮብኝ ነው። እነርሱም ምንም ሕመም ስለሌለባቸው፥ ሰውነታቸው ጤናማና ወዛም ነው። እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም፤ በሌሎች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ በእነርሱ ላይ አይደርስም። ስለዚህ ትዕቢትን እንደ ድሪ አጥልቀዋል፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ለብሰዋል። አእምሮአቸው ክፉ ሐሳብን እያፈለቀ ከዐይነ ስባቸው የሚወጡት ዐይኖቻቸው አፍጥጠው ይመለከታሉ። በሌሎች ሰዎች ላይ እያፌዙ የተንኰል ንግግርን ይናገራሉ፤ በትዕቢታቸውም የመጨቈን ዛቻን ይዝታሉ። በእግዚአብሔር ላይ መናገርን ይዳፈራሉ፤ በምድር ላይ ከመናገርም አያቆሙም። የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ወደ እነርሱ ያዘነብላሉ፤ የሚነግሩአቸውንም ሁሉ ይቀበላሉ። እነርሱም “በውኑ እግዚአብሔር ያውቃልን? ልዑል እግዚአብሔርስ ዕውቀት አለውን?” ይላሉ። እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው። ዘወትርም ተጨማሪ ሀብት ያገኛሉ።