የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 61:1-4

መጽሐፈ መዝሙር 61:1-4 አማ05

አምላክ ሆይ! ጩኸቴን አድምጥ፤ ጸሎቴንም ስማ። ተስፋ ቈርጬ ሳለ ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ከእኔ በላይ ወደ አለው ከፍተኛ አምባ ምራኝ። አንተ ጠባቂዬና ከጠላቶቼ የምከለልብህ ብርቱ መጠጊያዬ ነህ። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በቤትህ እንድኖርና በጥበቃህ ሥር መጠለያ እንዳገኝ ፍቀድልኝ።