እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ። እግዚአብሔር ሆይ! ደካማ ስለ ሆንኩ ምሕረት አድርግልኝ፤ ጌታ ሆይ! ደካማ ሰውነቴ እየተሠቃየ ስለ ሆነ፥ እባክህ ፈውሰኝ። እግዚአብሔር ሆይ! ሰውነቴ በሙሉ እጅግ ታውኮአል፤ ታዲያ፥ እኔን ከመርዳት የምትዘገየው እስከ መቼ ነው? እግዚአብሔር ሆይ! ተመልሰህ ታደገኝ፤ የዘለዓለም ፍቅርህን በማሳየት አድነኝ። ከሞቱት መካከል አንድም የሚያስታውስህ የለም። በመቃብርስ ሆኖ የሚያመሰግንህ ማነው? ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል። ከጠላቶቼ ተቃውሞ የተነሣ በጣም በማልቀሴ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤ ማየትም ተስኖኛል።
መጽሐፈ መዝሙር 6 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 6:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos