መጽሐፈ መዝሙር 6
6
1እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አትገሥጸኝ፤
በመዓትህም አትቅጣኝ። #መዝ. 38፥1።
2እግዚአብሔር ሆይ! ደካማ ስለ ሆንኩ ምሕረት አድርግልኝ፤
ጌታ ሆይ! ደካማ ሰውነቴ እየተሠቃየ ስለ ሆነ፥
እባክህ ፈውሰኝ።
3እግዚአብሔር ሆይ! ሰውነቴ በሙሉ እጅግ ታውኮአል፤
ታዲያ፥ እኔን ከመርዳት የምትዘገየው እስከ መቼ ነው?
4እግዚአብሔር ሆይ! ተመልሰህ ታደገኝ፤
የዘለዓለም ፍቅርህን በማሳየት አድነኝ።
5ከሞቱት መካከል አንድም የሚያስታውስህ የለም።
በመቃብርስ ሆኖ የሚያመሰግንህ ማነው?
6ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤
ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ
በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤
ትራሴም ይርሳል።
7ከጠላቶቼ ተቃውሞ የተነሣ
በጣም በማልቀሴ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤
ማየትም ተስኖኛል።
8እግዚአብሔር የለቅሶዬን ጩኸት ሰምቶአል፤
ስለዚህ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ! #ማቴ. 7፥23፤ ሉቃ. 13፥27።
9እግዚአብሔር ልመናዬን ያዳምጣል፤
እግዚአብሔር ለጸሎቴ መልስ ይሰጣል።
10ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤
በድንገትም ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይሸሻሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 6: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997