የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 32:1-5

መጽሐፈ መዝሙር 32:1-5 አማ05

ኃጢአታቸው ይቅር የተባለላቸውና በደላቸውም የተሰረየላቸው ሰዎች የተባረኩ ናቸው። እግዚአብሔር ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ከሽንገላም የራቀ ሰው የተባረከ ነው። ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በቀረሁ ጊዜ ቀኑን ሙሉ በመቃተቴ መላ ሰውነቴ ደከመ። ቀንና ሌሊት በብርቱ ቀጣኸኝ፤ ርጥበት ያለው ነገር በበጋ ሙቀት እንደሚደርቅ ጒልበቴ በፍጹም አለቀ። በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤ ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤ አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።