መጽሐፈ መዝሙር 23
23
እግዚአብሔር እረኛዬ ስለ ሆነ
1እግዚአብሔር እረኛዬ ስለ ሆነ፥
የሚያስፈልገኝን ሁሉ አላጣም።
2በለመለመ መስክ እንዳርፍ ያደርገኛል፤
ሰላማዊ ወደ ሆነ የውሃ ጅረትም ይመራኛል። #ራዕ. 7፥17።
3ሕይወቴን ያድሳል፤
ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።
4በጣም ጨለማ በሆነ
ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ
አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥
ምንም ክፉ ነገር አልፈራም።
ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።
5በጠላቶቼ ፊት ታላቅ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤
ራሴን በዘይት ትቀባልኛለህ፤
ጽዋዬም እስኪትረፈረፍ ድረስ ይሞላል።
6በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ደግነትና ፍቅር ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ይሆናሉ፤
በምኖርበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖራለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 23: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997