እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ እጁን በመዘርጋት ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ። በጣም በርትተውብኝ ከነበሩት ከኀይለኞች ጠላቶቼና ከሚጠሉኝ ሰዎች ሁሉ እጅ እግዚአብሔር አዳነኝ። እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ። ወደ ሰፊ ቦታ አወጣኝ፤ በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄም ንጽሕና ይመልስልኛል። እኔ የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትዬአለሁ፤ ፊቴን ከአምላኬ በመመለስ ክፉ ነገር አላደረግሁም። የእግዚአብሔርን ሕጎች ሁሉ እፈጽማለሁ ሥርዓቱንም ከማክበር ወደ ኋላ አላልኩም። በእርሱ ዘንድ ንጹሕ ነበርኩ፤ ከኃጢአትም ራሴን ጠብቄአለሁ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና፥ ዋጋዬን ከፈለኝ። አምላክ ሆይ! ለአንተ ታማኞች ለሆኑት ታማኝ ነህ፤ እውነተኞች ለሆኑትም እውነተኛ ነህ። ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፤ ለጠማሞች ግን ተገቢ ዋጋቸውን ትሰጣለህ። ትሑቶችን ታድናለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ታዋርዳለህ። እግዚአብሔር ሆይ! ለእኔ ብርሃኔ ነህ፤ አንተ አምላኬ ጨለማዬን ታበራለህ። በአንተ ርዳታ አንድ የጦር ጓድ አጠቃለሁ፤ አንተ አምላኬም ቅጥሩን ለመዝለል ትረዳኛለህ። የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው! ቃሉም ተጠራ ነው! እርሱን መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ማነው አምላክ? ከእርሱስ በቀር መጠጊያ የሚሆን ማነው? ብርታትን የሚሰጠኝና መንገዴን የሚያቀናልኝ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያጠነክራል፤ በከፍታ ቦታዎችም ያለ ስጋት ለመቆም ያስችለኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ የነሐስን ቀስት መሳብ እንዲችሉ ክንዶቼን ያበረታል። የማዳን ጋሻህን ሰጠኸኝ፤ ቀኝ እጅህም ይጠብቀኛል፤ እኔን ለመርዳት መጥተህ ታላቅ አደረግኸኝ። መረማመጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
መጽሐፈ መዝሙር 18 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 18:16-36
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos