መጽሐፈ መዝሙር 146
146
ለአዳኙ አምላክ የሚቀርብ ምስጋና
1እግዚአብሔር ይመስገን!
ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
2በሕይወቴ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
3ማዳን ስለማይችሉ በመሪዎች
ወይም በማንኛውም ፍጡር አትተማመኑ።
4እነርሱ በሚሞቱበት ጊዜ ወደ ዐፈር ይመለሳሉ፤
በዚያኑ ቀን ዕቅዳቸው ሁሉ ይጠፋል።
5የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነለትና
በአምላኩ በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረገ ሰው ደስ ይበለው፤
6እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፥
ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ የፈጠረ ነው።
እርሱ ዘወትር ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤ #ሐ.ሥ. 4፥24፤ 14፥15።
7ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል፤
ለተራቡ ምግብን ይሰጣል።
እስረኞችን ነጻ ያወጣል።
8የዕውሮችን ዐይን ያበራል፤
የወደቁትን ያነሣል፤
ጻድቃንን ይወዳል።
9እግዚአብሔር መጻተኞችን ይጠብቃል፤
ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና
ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆች ይረዳል፤
የክፉዎችን ዕቅድ ግን ያፈርሣል።
10እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ነው፤
ጽዮን ሆይ አምላክሽ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይነግሣል።
እግዚአብሔር ይመስገን!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 146: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997