መጽሐፈ መዝሙር 144:1-3

መጽሐፈ መዝሙር 144:1-3 አማ05

መጠጊያዬ እግዚአብሔር ይመስገን! ለሰልፍ ያሠለጥነኛል፤ ለጦርነትም ያዘጋጀኛል። እግዚአብሔር ጠባቂዬና መከታዬ ነው፤ መጠለያዬና አዳኜ ነው፤ በእርሱ ተማምኜ በሰላም እኖራለሁ፤ እርሱ አሕዛብን ከእግሬ በታች አድርጎ ያስገዛልኛል። እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ያኽል የምትንከባከበው ሰው ምንድን ነው? ይህን ያኽልስ የምታስብለት የሰው ልጅ ምንድን ነው?