መጽሐፈ መዝሙር 142
142
የእግዚአብሔርን ርዳታ ለማግኘት የሚቀርብ ጸሎት
1ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር
እጮኻለሁ፤
ምሕረት እንዲያደርግልኝ እለምነዋለሁ።
2አቤቱታዬን ሁሉ በፊቱ አቀርባለሁ፤
ችግሬንም ሁሉ እነግረዋለሁ።
3ተስፋ ለመቊረጥ ጥቂት በቀረኝ ጊዜ
ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ያውቃል፤
ጠላቶቼ በምሄድበት መንገድ ላይ
ወጥመድ ዘረጉብኝ።
4በዙሪያዬ ስመለከት መሸሸጊያ የሚሆነኝ አጣሁ፤
አንድም እንኳ የሚረዳኝ ሰው አልነበረም፤
የሚጠብቀኝና የሚጠነቀቅልኝም አልነበረም።
5እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ
ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ! ጠባቂዬ አንተ ነህ፤
በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ።
6በጣም ተስፋ የቈረጥሁ ስለ ሆነ
እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮኽ ስማኝ፤
እጅግ በርትተውብኛልና ከጠላቶቼ አድነኝ።
7አመሰግንህ ዘንድ ከእስራቴ አውጣኝ፤
ለእኔ ያደረግኸውን ያንተን የቸርነት ሥራ በሚያዩበት ጊዜ
ሕዝብህ በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ። #1ሳሙ. 22፥1፤ 24፥3።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 142: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997