የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 132

132
ስለ ቤተ መቅደስ የቀረበ ውዳሴ
1እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዳዊትን አስታውሰው፤
የተቀበለውን መከራ ሁሉ አትርሳ።
2እግዚአብሔር ሆይ! ለአንተ የገባውን ቃል ኪዳንና
ሁሉን ለምትችል ለያዕቆብ አምላክ ለአንተ
እንዲህ ሲል የተሳለውን ስእለት አስታውስ፤
3-5“ለእግዚአብሔር የመኖሪያ ስፍራ እስከማዘጋጅ፥
ለያዕቆብ አምላክ ቤት እስከምሠራ ድረስ፥
ወደ ቤት አልገባም፤
ወይም በአልጋ ላይ አልተኛም፤
ዕረፍት ወይም እንቅልፍ አይኖረኝም።”
6በኤፍራታ ሆነን ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት ሰማን፤
በጁአሪም ምድር አገኘነው።
7ከዚህ በኋላ “ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ፤
በእግሩ ማረፊያ ሥር እንስገድ” አልን።
8እግዚአብሔር ሆይ!
የኀይልህ መግለጫ ከሆነችው
ከቃል ኪዳን ታቦት ጋር ወደምታርፍበት
ወደ ቤተ መቅደስ ግባ።
9ካህናትህ የጽድቅን ሥራ ይሥሩ!
ታማኞችህ በደስታ ይዘምሩ!
10ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል
መርጠህ የቀባኸውን አትተወው። #2ዜ.መ. 6፥41-42።
11እግዚአብሔር ለዳዊት እንዲህ ሲል
የማይሻር ቃል ኪዳን ገባለት፦
“ከልጆችህ አንዱን አነግሠዋለሁ፤ #2ሳሙ. 7፥12-16፤ 1ዜ.መ. 17፥11-14፤ መዝ. 89፥3-4፤ ሐ.ሥ. 2፥30።
12ልጆችህ ቃል ኪዳኔንና የምሰጣቸውን
ትእዛዞች ከጠበቁ
ልጆቻቸው ከአንተ በኋላ
ለዘለዓለም ይነግሣሉ።”
13እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል፤
መኖሪያውም ሊያደርጋት ይፈልጋል።
14ይህች የዘለዓለም ማረፊያ ስፍራዬ ናት፤
በዚያች ለመኖር እመኝ ስለ ነበር
መኖሪያዬ አደረግኋት።
15ለጽዮን ምግብዋን አበዛለሁ፤
ድኾችዋንም እስከሚጠግቡ አበላቸዋለሁ።
16ካህናትዋን በሚያደርጉት ሁሉ እባርካቸዋለሁ፤
በውስጥዋም የሚኖሩ ታማኞች በደስታ ይዘምራሉ።
17ከዳዊት ዘር ንጉሥ እንዲወጣ አደርጋለሁ፤
የቀባሁትንም ኀያል አደርገዋለሁ። #1ነገ. 11፥36።
18ጠላቶቹ ኀፍረትን እንዲከናነቡ አደርጋቸዋለሁ፤
እርሱ ግን የሚያንጸባርቅ ዘውድ ይቀዳጃል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ