መጽሐፈ መዝሙር 126
126
ከምርኮ በደስታ ስለ መመለስ የቀረበ ምስጋና
1እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ
ባመጣን ጊዜ ሕልም እንጂ
እውነት አልመሰለንም ነበር።
2አፋችን በሳቅ ተሞላ፤
አንደበታችንም የደስታ መዝሙር ዘመረ፤
በዚህም ምክንያት አሕዛብ፦
“እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” አሉን።
3በእርግጥም ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርጎልናል፤
እጅግም ተደስተናል።
4እግዚአብሔር ሆይ!
ዝናብ ለደቡብ በረሓ ወንዝ ውሃን እንደሚሰጥ
የተማረከብን ሀብታችንን መልስልን።
5በእንባ የሚዘሩ
የደስታ መዝሙር እየዘመሩ ይሰበሰባሉ።
6ዘሩን ተሸክመው ሲሄዱ ያለቅሱ የነበሩት፥
በደስታ እየዘመሩ ነዶአቸውን ተሸክመው ይመለሳሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 126: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997