መጽሐፈ መዝሙር 124
124
እግዚአብሔር ወገኖቹን የሚጠብቅ መሆኑ
1እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን
ምን ይበጀን ነበር?
እስራኤል እንዲህ ብሎ ይመልስ፤
2“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን
ጠላቶቻችን ባጠቁን ጊዜ
3በታላቅ ቊጣ በእኛ ላይ ተነሥተው
ከነሕይወታችን በዋጡን ነበር፤
4ጐርፍ በወሰደን፥ ውሃም በሸፈነን ነበር፤
5ብርቱ ማዕበልም ባሰጠመን ነበር።”
6ጠላቶቻችን እንዲደመስሱን ያላደረገ
እግዚአብሔር ይመስገን።
7እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አምልጠናል፤
ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም ነጻ ወጣን።
8ይህንንም ርዳታ ያገኘነው
ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 124: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997