መጽሐፈ መዝሙር 118:5-9

መጽሐፈ መዝሙር 118:5-9 አማ05

በተጨነቅሁ ጊዜ ጩኸቴን ወደ እግዚአብሔር አሰማሁ፤ እርሱም ሰማኝ፤ ነጻም አወጣኝ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ አልፈራም፤ ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል? እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ፥ የጠላቶቼን ውድቀት አያለሁ። በሰው ከመመካት ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል። በመሪዎች ከመመካት ይልቅ፥ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።