መጽሐፈ መዝሙር 108
108
የእግዚአብሔርን ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
(መዝ. 57፥7-11፤ 60፥5-12)
1አምላኬ ሆይ! ልቤ ጽኑ ነው፤
ነቅቼ በሁለንተናዬ እዘምራለሁ፤
በዜማ አመሰግንሃለሁ።
2በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ፤
እኔም በማለዳ እነሣለሁ።
3እግዚአብሔር ሆይ! በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤
በአሕዛብ መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
4ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው፤
ታማኝነትህም ወደ ጠፈር ይደርሳል።
5አምላክ ሆይ! ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤
ክብርህም ከምድር ሁሉ በላይ ይሁን።
6የምትወደው ሕዝብህ ይድን ዘንድ፥
ጸሎታችንን ስማ፤ በኀይልህም ታደገን።
7እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፦
“ድል አድርጌ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤
የሱኮትንም ሸለቆ ለሕዝቤ አከፋፍላለሁ።
8ገለዓድና ምናሴ የእኔ ናቸው፤
ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቊር ነው፤
ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።
9ሞአብ መታጠቢያዬ ነው፤
ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤
በፍልስጥኤማውያንም ላይ በድል አድራጊነት እደነፋለሁ።”
10አምላክ ሆይ! ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?
እስከ ኤዶምስ ማን ይመራኛል?
11አምላክ ሆይ! አንተ ጥለኸናል፤
ከሠራዊታችንም ጋር ወደ ጦር ሜዳ መውጣት ትተሃል።
12የሰው ርዳታ ከንቱ ነው፤
ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ እርዳን።
13እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ እናሸንፋለን፤
እርሱ ጠላቶቻችንን ያዋርዳቸዋል።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 108: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997