አንዳንዶች በመርከብ ተሳፍረው በታላቅ በባሕር ላይ እየተጓዙ ንግዳቸውን ያካሂዱ ነበር። እነርሱ የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ አዩ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ ተመለከቱ። ትእዛዝ በሰጠ ጊዜ ዐውሎ ነፋስ ነፈሰ፤ ማዕበሉም ተንቀሳቀሰ። መርከበኞቹ በሞገዱ ኀይል ተገፍትረው ወደ ላይ ወጡ፤ ተመልሰውም ወደ ጥልቁ ወረዱ፤ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ተዋከቡ። እንደ ሰካራም ዞረባቸው፤ ተንገዳገዱም፤ የማስተዋል ችሎታቸው ሁሉ ጠፋ። በመከራቸው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከጭንቀታቸው አዳናቸው። ዐውሎ ነፋሱንና ማዕበሉን ጸጥ አደረገ። በጸጥታውም ምክንያት ደስ አላቸው፤ ወደ ፈለጉትም ወደብ በሰላም አደረሳቸው። ስላደረገላቸው ድንቅ ነገሮችና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የሰው ልጆች እግዚአብሔርን ያመስግኑ። በሕዝብ ጉባኤ መካከል ታላቅነቱንም ያብሥሩ፤ በሽማግሌዎች ሸንጎ ያመስግኑት። እግዚአብሔር ወንዞች ፈጽመው እንዲደርቁ፥ ምንጮችም እንዳይፈስሱ አደረገ። እዚያ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን አገር እንደ ጨው ምድር የማታፈራ አደረጋት። እንደገናም በበረሓው ብዙ ኲሬዎች እንዲኖሩ፥ በደረቁም ምድር ብዙ ምንጮች እንዲገኙ አደረገ። የተራቡ ሕዝቦች በዚያ እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሠሩ። በእርሻዎች ላይ እህልን ዘሩ፤ ወይንን ተከሉ፤ ብዙ መከርም ሰበሰቡ። ሕዝቡን ባረካቸው፤ ብዙ ልጆችም ወለዱ፤ የከብቶቻቸውም ቊጥር እንዳያንስ አደረገ። በጭቈና፥ በችግርና በሐዘን ተሸንፈው በተዋረዱ ጊዜ ግን፥ እግዚአብሔር ልዑላኑን አዋረደ፤ በምድረ በዳም አሸዋ ውስጥ እንዲንከራተቱ አደረገ። ችግረኞችንም ከሥቃያቸው አወጣቸው፤ እንደ በግ መንጋ የበዙ ልጆችንም ሰጣቸው። ቅኖች ይህን በማየት ደስ ይላቸዋል፤ ክፉዎች ግን ዐፍረው ዝም ይላሉ። ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ ይህን ያስተውሉ፤ ዘለዓለማዊውን የእግዚአብሔርን የፍቅር ሥራ ይገንዘቡ።
መጽሐፈ መዝሙር 107 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 107:23-43
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos