የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 6:1-11

መጽሐፈ ምሳሌ 6:1-11 አማ05

ልጄ ሆይ! ዕዳውን ለመክፈል ለማይችል ሰው አንተ ልትከፍልለት ቃል ብትገባ፥ በተናገርከው ንግግር ብትጠመድ፥ በገባኸውም ቃል ብትያዝ፥ ልጄ ሆይ! በዚያ ሰው ሥልጣን ሥር ሆነሃል ማለት ነው፤ ስለዚህ ከእርሱ ቊጥጥር ነጻ ለመውጣት ብትፈልግ ፈጥነህ ወደ እርሱ ሂድ፤ ዋስትናውንም እንዲያወርድልህ ለምነው። ይህንን ሳታደርግ አትተኛ፤ በዐይንህም እንቅልፍ አይዙር። ሚዳቋ ከአዳኝ እጅ፥ ወፍ ከወጥመድ እንደሚያመልጡ አንተም ራስህን አድን። አንተ ሰነፍ ወደ ጒንዳን ሄደህ መንገድዋን ተመልክተህ ጥበብን ቅሰም። ጒንዳኖች መሪ፥ አለቃ፥ ወይም ገዢ የላቸውም፤ ነገር ግን በበጋ ወራት ምግባቸውን ያከማቻሉ፤ በመከር ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ይሰበስባሉ። ታዲያ፥ አንተ ሰነፍ! የምትተኛው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህስ የምትነቃው መቼ ነው? “ጥቂት እተኛለሁ፤ ጥቂት አንቀላፋለሁ፤ እጄንም አጣጥፌ ለጥቂት ጊዜ ዐርፋለሁ” ስትል፥ ገና ተኝተህ ሳለ ድኽነትና ማጣት የጦር መሣሪያ እንደ ታጠቀ ወንበዴ በድንገት ይደርሱብሃል።