ኦሪት ዘኊልቊ 21:4-5

ኦሪት ዘኊልቊ 21:4-5 አማ05

እስራኤላውያን በኤዶም ግዛት ዙሪያ ለመሄድ አስበው ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ነገር ግን በመንገድ ሳሉ የሕዝቡ ትዕግሥት አለቀ፤ በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ክፉ ቃል በመናገር እንዲህ ሲሉ አጒረመረሙ፤ “ምግብና ውሃ በሌለበት በዚህ በረሓ እንሞት ዘንድ ከግብጽ ምድር ለምን አወጣችሁን? ይህን አስከፊ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል!”