የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ነህምያ 2:17-18

መጽሐፈ ነህምያ 2:17-18 አማ05

ከዚህ በኋላ ግን “እንግዲህ ያለውን ችግር ሁሉ ተመልከቱት! ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ሆናለች፤ የቅጽር በሮችዋም በእሳት ወድመዋል፤ ስለዚህ ተነሥተን የከተማይቱን ቅጽሮች እንሥራ፤ የደረሰብንንም ኀፍረት እናስወግድ” አልኳቸው። ቀጠል አድርጌም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑንና እንዴትም እንደ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱም የነገረኝን ሁሉ ገለጥሁላቸው። እነርሱም “እንደገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉኝ በኋላ፥ ይህን በጎ ሥራ ለመጀመር ተዘጋጁ።