እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁም ይህን ስሙ! በምድር ላይ የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ! ጌታ እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ሆኖ ያጋልጣችኋል። እነሆ፥ እግዚአብሔር ከቦታው ወጥቶ ይመጣል፤ ወርዶም በምድር ከፍታ ቦታዎች ላይ ይራመዳል። በዚያን ጊዜ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥና፥ ውሃም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ታች እንደሚወርድ እንዲሁም ተራራዎች ከእርሱ ሥር ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይከፈታሉ። ይህ ሁሉ የሆነው እስራኤላውያን በፈጸሙት በደል ምክንያት ነው፤ የእስራኤል ሕዝብ እንዲያምፁ ምክንያት የሆነው ማን ነው? ዋና ከተማዋ ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ ሕዝብ ጣዖት በማምለክ ኃጢአት እንዲሠሩ ያደረገ ማን ነው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን? ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ሰማርያን በሜዳ ላይ እንደሚታይ የቤት ፍርስራሽ ክምር አደርጋለሁ፤ የወይን መትከያ ቦታ ትሆናለች፤ የከተማይቱንም ፍርስራሽ ድንጋይ ወደ ሸለቆ አፈሰዋለሁ፤ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ። ምስሎችዋ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለመቅደስዋ አመንዝሮች የተከፈለውም ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ፤ ጣዖቶችዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፤ ሰማርያ እነዚህን ምስሎች የሰበሰበቻቸው የዝሙት ዋጋ መቀበያ ለማድረግ ነበር፤ አሁንም ጠላቶችዋ የዝሙት መጠቀሚያ ያደርጉአቸዋል።”
ትንቢተ ሚክያስ 1 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ሚክያስ 1:2-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos