የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማቴዎስ ወንጌል 18:10-22

የማቴዎስ ወንጌል 18:10-22 አማ05

በሰማይ ያሉት መልአኮቻቸው ዘወትር በሰማይ ያለውን ያባቴን ፊት ስለሚያዩ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ። [ የሰው ልጅም የመጣው የጠፋውን ለማዳን ነው።”] ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እስቲ ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋውን አንዱን ለመፈለግ አይሄድምን? እውነት እላችኋለሁ፤ ባገኘው ጊዜ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ ጠፍቶ በተገኘው በግ ደስ ይለዋል። እንዲሁም በሰማይ ያለው አባታችሁ ከነዚህ ከታናናሾች አንዱም እንዲጠፋ አይፈልግም። “ወንድምህ ቢበድልህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ በደሉን ንገረው፤ ቢሰማህ እንደገና ወንድምህ እንዲሆን ታደርገዋለህ፤ ባይሰማህ ግን የሁለት ወይም የሦስት ሰዎች ምስክርነት ስለሚጸና ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ይዘህ ወደ እርሱ ሂድ። እነርሱንም አልሰማም ቢል ለቤተ ክርስቲያን ንገር፤ ቤተ ክርስቲያንንም የማይሰማ ከሆነ እንደ አረመኔና ተጸጽቶ እንደማይመለስ ኃጢአተኛ ቊጠረው። “በእውነት እላችኋለሁ፤ በምድር የምታስሩት በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱትም በሰማይ የተፈታ ይሆናል። ደግሞም እላችኋለሁ፤ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ላይ ማናቸውንም ነገር ለመለመን ተስማምተው ቢጸልዩ፥ በሰማይ ያለው አባቴ ይፈጽምላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት ስፍራ እኔ በመካከላቸው እገኛለሁ።” በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፦ “ጌታ ሆይ! ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም፤

ተዛማጅ ቪዲዮዎች