የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሚልክያስ 3:13-18

ትንቢተ ሚልክያስ 3:13-18 አማ05

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእኔ ላይ የድፍረት ቃል ትናገራላችሁ፤ እንደገና ደግሞ ‘እኛ በአንተ ላይ ምን ክፉ ነገር ተናገርን?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ እናንተ ‘እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዞቹን መጠበቅና እንደ ሐዘንተኞች በሠራዊት አምላክ ፊት መመላለስ ምን ይጠቅመናል? እንደምናየው ከሆነ እነሆ፥ ክፉ አድራጊዎች ዕድለኞች ናቸው፤ በእርግጥም እነርሱ በብልጽግና ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርን እንኳ እየተፈታተኑት ምንም ችግር አይደርስባቸውም እያላችሁ ትናገራላችሁ።’ ” ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም በጥሞና አዳመጣቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩና ስሙንም የሚያከብሩ ሰዎች ለተግባራቸው መታሰቢያ በመጽሐፍ ተጻፈ። የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ የግሌ ይሆናሉ፤ ወላጆች ለሚያገለግሉአቸው ልጆች ምሕረት እንደሚያደርጉላቸው እኔም ለእነርሱ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ። በዚያን ጊዜ በጻድቅና በኃጢአተኛ ለእግዚአብሔር በሚታዘዝና በማይታዘዝ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት እንደገና ታያላችሁ።”