የሉቃስ ወንጌል 8:19-21

የሉቃስ ወንጌል 8:19-21 አማ05

የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ ወደ እርሱ መጡ፤ ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሊያገኙት አልቻሉም። ስለዚህ “እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ በውጪ ቆመው ሊያዩህ ይፈልጋሉ፤” ብለው ሰዎች ነገሩት። ኢየሱስም “የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚፈጽሙት ሁሉ እነርሱ እናቴና ወንድሞቼ ናቸው፤” አለ።