የሉቃስ ወንጌል 22:1-6

የሉቃስ ወንጌል 22:1-6 አማ05

ፋሲካ የተባለው የቂጣ በዓል የሚከበርበት ቀን ተቃርቦ ነበር፤ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሕዝቡን ስለ ፈሩ ኢየሱስን ይዘው የሚገድሉበትን ዘዴ በስውር ይፈልጉ ነበር። በዚያን ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ በሆነው በአስቆሮታዊው ይሁዳ ሰይጣን ገባበት። ስለዚህ ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደስ ዘብ አዛዦች ሄዶ ኢየሱስን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ። እነርሱም በነገሩ ተደስተው ገንዘብ ሊሰጡት ተዋዋሉ። በውሉ ተስማምቶ ሕዝቡ ሳያውቅ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።