የሉቃስ ወንጌል 12:10-12

የሉቃስ ወንጌል 12:10-12 አማ05

“በሰው ልጅ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር በደሉ ይቅር ይባልለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር ግን በደሉ ይቅር አይባልለትም። “ሰዎች በየምኲራቡ ሲወስዱአችሁ፥ በገዢዎችና በባለሥልጣኖች ፊት ለፍርድ ሲያቀርቡአችሁ ‘ምን እንመልሳለን? እንዴትስ እንናገራለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ። ልትናገሩት የሚገባችሁን በዚያን ሰዓት መንፈስ ቅዱስ ይነግራችኋል።”