ማርያምም እንዲህ አለች፦ “ነፍሴ ጌታን ታመሰግናለች፤ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ትደሰታለች፤ እግዚአብሔር እኔን ዝቅተኛ አገልጋይቱን ተመልክቶአልና፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ ይሉኛል፤ ኀያሉ እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን አድርጎልኛልና። ስሙም ቅዱስ ነው። እግዚአብሔር ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ ከትውልድ እስከ ትውልድ ምሕረቱን ያደርጋል። በብርቱ ክንዱ ኀይሉን አሳይቶአል፤ ትዕቢተኞችንም ከነሐሳባቸው በትኖአቸዋል። ታላላቅ ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአቸዋል፤ ዝቅተኞችን ግን በክብር ከፍ አድርጎአቸዋል። የተራቡትን በመልካም ነገር አጥግቦአቸዋል፤ ሀብታሞችን ግን ባዶ እጃቸውን ሰዶአቸዋል፤ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘለዓለም ያሳየውን ምሕረት በማስታወስ፥ አገልጋዩን እስራኤልን ረድቶታል። ይህንንም ያደረገው ለቀድሞ አባቶቻችን የሰጠውን የተስፋ ቃል ለመፈጸም ነው።”
የሉቃስ ወንጌል 1 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 1:46-55
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos