የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኢዩኤል 3

3
እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥
“በዚያን ጊዜ የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ምርኮ እመልሳለሁ፤
2አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ፥
ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤
የእኔ የሆኑትን ሕዝቤን እስራኤልን
በሕዝቦች መካከል ስለ በታተኑና ምድሪቱን ስለ ተካፈሉ
በኢዮሣፍጥ ሸለቆ ወደ ፍርድ አቀርባቸዋለሁ። #3፥2 ኢዮሣፍጥ፦ በእብራይስጥ እግዚአብሔር ይፈርዳል ማለት ነው።
3የማረኩአቸውን ሕዝቤንም ለመከፋፈል ዕጣ ተጣጥለዋል፤
አመንዝራ ሴቶችን ለማግኘት ወንዶች ልጆችን ሰጡ፤
ወይን ጠጅ ለመጠጣትም ሴቶች ልጆችን ባሪያ አድርገው ሸጡ።
4“እናንተ የጢሮስ፥ የሲዶናና የፍልስጥኤም አውራጃዎች ሕዝብ ሆይ፥ ምን እያደረጋችሁ ነው? እኔን ለመበቀል ይቃጣችኋልን? ይህ ከሆነ ሥራችሁ ወዲያው በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እንዲመለስ አደርጋለሁ። #ኢሳ. 14፥29-31፤ 23፥1-18፤ ኤር. 47፥1-7፤ ሕዝ. 25፥15—28፥26፤ አሞጽ 1፥6-10፤ ሶፎ. 2፥4-7፤ ዘካ. 9፥1-7፤ ማቴ. 11፥21-22፤ ሉቃ. 10፥13-14። 5ብሬንና ወርቄን እንዲሁም ውድ የሆነ ሀብቴን ሁሉ ወስዳችሁ ወደ ጣዖት ማምለኪያ ቤታችሁ አስገብታችኋል። 6የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ተወላጆች ከአገራቸው ድንበር አርቃችሁ በመውሰድ ለግሪክ ሰዎች ሸጣችኋል። 7እነሆ አሁን ከተሸጡባቸው ስፍራዎች አነሣሥቼ እንዲወጡ አደርጋለሁ፤ በእነርሱ ላይ የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ በእናንተ ላይ መልሼ አመጣባችኋለሁ። 8የእናንተንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ለይሁዳ ሕዝብ ተላልፈው እንዲሸጡ አደርጋለሁ፤ እነርሱም ሩቅ ላሉት ለሳባውያን ይሸጡአቸዋል፤ ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
9“ይህን ለአሕዛብ ሁሉ ዐውጁ፤
ለጦርነት ተዘጋጁ፤
ጀግኖችን ቀስቅሱ፤
ጦረኞቻችሁ ሁሉ ተሰብስበው ለጦርነት ይሰለፉ።
10ማረሻችሁ ሰይፍ፥ ማጭዳችሁም ጦር እንዲሆን ቀጥቅጡ፤
ደካማውም እንኳ ‘እኔ ብርቱ ነኝ’ ይበል፤ #ኢሳ. 2፥4፤ ሚክ. 4፥3።
11እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፤
በፍጥነት ውጡ!
በሸለቆውም ተሰብሰቡ።”
እግዚአብሔር ሆይ፥ ተዋጊ ሠራዊትህን ላክ።
12“አሕዛብ ሁሉ ተነሣሥተው ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ ይሂዱ፤
እኔ እግዚአብሔር በዙሪያ ባሉት አሕዛብ ላይ ለመፍረድ
እዚያ እቀመጣለሁ።
13የእነርሱ ክፋት እጅግ በዝቶአል፤
የደረሰ መከር በማጭድ እንደሚታጨድ እጨዱአቸው፤
የወይን ዘለላ በመጥመቂያው ሞልቶ እንደሚረገጥ ርገጡአቸው፤” #ራዕ. 14፥14-16፤19-20፤ 19፥15።
14ጌታ በፍርድ ሸለቆ ፍርድ የሚሰጥበት ቀን ደርሶአል፤
ስለዚህ ቊጥሩ እጅግ የበዛ ሕዝብ በዚያ ተሰብስቦአል።
15በዚያን ቀን ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤
ከዋክብትም ብርሃናቸውን ያጣሉ።
16እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በኢየሩሳሌም ሆኖ፥
የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤
ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤
እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ለእስራኤል
መጠጊያ ምሽግ ይሆናል፤
እግዚአብሔር ሕዝቡን መባረኩ #አሞጽ 1፥2
17“እስራኤል ሆይ! በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር
አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ፤
በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ እኖራለሁ፤
ኢየሩሳሌምም የተቀደሰች ከተማ ትሆናለች፤
ከእንግዲህ ወዲህ የባዕድ ወታደሮች አይወሩአትም።
18“በዚያን ጊዜ ተራራዎችም ሁሉ በወይን ተክል ይሸፈናሉ፤
በኰረብቶችም ላይ ብዙ ወተት የሚሰጡ ከብቶች ይሰማራሉ፤
በይሁዳ ምድር የሚገኙ ወንዞች ሁሉ በውሃ የተሞሉ ይሆናሉ፤
ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ምንጭ ይፈልቃል፤
የሺጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።
19“የግብጽና የኤዶም ሰዎች በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለ ፈጸሙና
ንጹሑንም ሕዝብ ስለ ገደሉ፥
‘ግብጽ ወደ በረሓነት ትለወጣለች፤
ኤዶምም ሰው የማይኖርባት ምድረ በዳ ትሆናለች።’
20-21ስለዚህ እስከ አሁን ድረስ ሳልበቀልላቸው የቀረሁትን
የንጹሐንን ደም እበቀላለሁ፤
ይሁዳና ኢየሩሳሌም ግን ለዘለዓለም ለሕዝቤ መኖሪያ ይሆናሉ፤
እኔም እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ እኖራለሁ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ