በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙር ወጡና ወደ መቃብሩ ሄዱ። ሁለቱም አብረው ይሮጡ ነበር፤ ነገር ግን ሌላው ደቀ መዝሙር ከጴጥሮስ ይበልጥ ፈጥኖ ሮጠና ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደረሰ። ጐንበስ ብሎም ወደ መቃብሩ ቢመለከት የከፈኑ ጨርቅ እዚያ ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አልገባም። ስምዖን ጴጥሮስም ተከትሎት መጣና ወደ መቃብሩ ውስጥ ገባ፤ እርሱም የከፈኑን ጨርቅ እዚያ ተቀምጦ አየ፤ የኢየሱስ ራስ ተጠምጥሞ የነበረበት ጨርቅ ከከፈኑ ጨርቅ ጋር ሳይሆን ለብቻው በሌላ ስፍራ ተጠቅሎ እንደ ተቀመጠ አየ። ቀጥሎም ያ ቀድሞ የደረሰው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብሩ ውስጥ ገብቶ አየና አመነ። “ከሞት መነሣት ይገባዋል” የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ገና አልተገነዘቡም ነበር። ከዚህ በኋላ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ተመልሰው ወደ ቤታቸው ሄዱ።
የዮሐንስ ወንጌል 20 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 20:3-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች