የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኤርምያስ 20:7-9

ትንቢተ ኤርምያስ 20:7-9 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! አታለልከኝ፤ እኔም ተታለልኩ፤ አንተ ከእኔ ትበረታለህ፤ ኀይልህም በእኔ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ሰው ሁሉ በየዕለቱ በማሽሟጠጥ ይዘባበትብኛል። እኔ በምናገርበት ጊዜ ሁሉ የምናገረው ዐመፅንና ጥፋትን ነው፤ አምላክ ሆይ! አንተ ያዘዝከኝን የትንቢት ቃል በመናገሬ፥ እኔ ዘወትር እሰደባለሁ፤ መላገጫም ሆኛለሁ። ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።